የጤና ተቋማትን በተመለከተ ከ22 ሺህ ገደማ ተቋማት መካከል 6 ሺህ ያህሉ ከለውጡ ወዲህ የተገነቡ ናቸው። የግል ዘርፍ የህክምና ተቋማትም እየተስፋፉ ነው። ሆኖም አሁንም ችግር አለ፣ ከመሰረተ ልማትና ከጤና ባለሙያዎች ጥያቄ አንጻር ምላሽ እየሰጠን መጓዝ ያስፈልጋል፤ ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህንን በማስፋት የጤና ስርዓቱን ማጠናከር ያስፈልጋል። በዚህ ዓመት 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ህጻናትን በቅድመ መደበኛ ትምህርት ተቀብለናል። 26 ሺህ ደግሞ የልዩ ፍላጎት ህጻናት ናቸው። በዚህ ልክ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች መገንባትና መምህራንን ማፍራት ላይም ሰርተናል። የመምህራን ልማትን በሚመለከት ወደ 68 ሺህ መምህራን ሰልጥነዋል፤ ዘንድሮ 80 ሺህ መምህራን በትምህርትና መማር ማስተማር ይሰለጥናሉ። 30 ገደማ ሞደል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እየተገነቡ ነው። ማህብረሰቡ በትምህርት ለትውልድ ባዋጠው ገንዘብ፤ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመፅሐፍና ትምህርት ጥምርታን ማሟላት ተችሏል። እነዘህን ተግባራት እያጠናከርን ስንሄድ ተጨባጭ ውጤት ይመጣል። #የጠሚሩምላሾች #PMOEthiopia